ወደ ማሳቹሴትስ ትምህርት ቤቶች እንኳን በደህና መጡ – ከማሳቹሴትስ የትምህርት ቤቶች አማራጮች ጋር እናስተዋውቃችኋለን።
ማሳቹሴትስ ግሩም ትምህርት ቤቶች እና በርካታ የትምህርት አማራጮች አሏት ።
እዚሀ የተገኘነው ለእያንዳንዱ ልጃችሁ ሊገኙ ስለሚችሉ አማራጮችና ክፍት እድሎች በቋንቋችሁ ልናነጋግራችሁ ነው።
ይህ ዝግጅት የታቀደው በፍልሰት ለመጡ ወላጆችና፣ እዚህ በማሳቹሴትስ ላለው የትምህርት ሥርዓት አዲስ ለሆኑ ሰዎች ነው ።
የሚታየን ፡ በግዛታችን ስላሉ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎች እና የትምህርት አማራጮች ዳሰሳ በማድረግ የቋንቋና ቴክኖሎጂ መሰናክሎች እንዲሁም ባህላዊ ልዩነቶችን በተቻለ መጠን ማስወገድ ነው።
[Welcome to Massachusetts Schools – Amharic]

